የሥራ ቃለ መጠይቅ / Interview/
ክፍል 1
የክረምት መዳረሻዎች እና ወራቶች ላይ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተማረ የሰው ኃይል ለሕዝብ የሚያስረክቡበት ነው። በመሆኑም አብዛኞቹ ተቋማት ከዚህ ወር ጀምሮ የቅጥር ቃለ መጠይቅ ያካሂዳሉ። ዘመኑ የውድድር መንፈስ የተጠናወተው ነውና ራስን ማዘጋጀት የብልህ ሰው መለያ ነው።
በሥራ ቃለ መጠይቅ /Interview/ ላይ በብዛት የሚጠይቁ ጥያቄዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል። እነሱም:-
1ኛ. ራስዎን ያስተዋውቁን?
(Please introduce yourself to know who you are?)
ይህ ጥያቄ ቀላል ቢመስልም፤ ብዙዎች ገና ከጅምሩ ስህተት የሚሰሩበት ነው። ብዙዎች የሕይወት ታሪካቸውን ያወራሉ። የጥያቄው አይን ግን በሥራ (በትምህርት) ሕይወት ላይ ስለቆያችሁበት ማንነት፣ የት/ት ደረጃ፣ የስራ ልምድ ካላችሁ ስለ ልምዳችሁ፣ ስላስመዘገባችሁት እና ስለ ሰራችሁት ጥሩ ሥራዎች፣ ጀማሪ ተቀጣሪ ከሆናችሁ ደግሞ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ስለ ነበራችሁ መልካም እንቅስቃሴዎች ወይም ስለ ሰራችሁት የመመረቂያ ጥናት (Research) ወይም ፕሮጀክት በመዘርዘር እራሳችሁን ማስተዋወቅ ነው። በንግግራችሁ ወቅት ለጠያቂው የመጀመሪያ ምርጫው እንድትሆኑ ጠቃሚ ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጉ። የዘር ሀረግ እየቆጠሩ፣ በትውልድ ቦታ እየከለላችሁ ጥያቄውን እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ። ለዚያውም በዚህች ጎጠኛ ዓለም ላይ ተሳታፊ ሆኖ ጎጥ መቁጠር ተገቢ አይደለም።
2ኛ. ስለዚህ የሥራ ማስታወቂያ እንዴት መረጃ አገኙ?
(How did you got an information about this vacancy?)
ይኸም በተደጋጋሚ ይጠየቃል። የዚህ ጥያቄ ዓላማው ድርጅቱን ምን ያክል እንደምትወዱትና እንደምትፈልጉት ለማወቅም ጭምር ነው። በመሆኑም መልሳችሁ “የድርጅቱን ድረገጽ እከታተል ስለነበር ከዛ ላይ አገኘው”፣ “ከጋዜጣ ላይ”፣ “ከማስታወቂያ ቦርድ ላይ” በማለት በትክክል መልሱ። ለመልሶቻችሁ ውበት ብላችሁ የሌለ ነገር ከጠቀሳችሁ ውሸታም ያስብላችኋል።
3ኛ. ስለ መስሪያ ቤታችን ምን ያውቃሉ?
(Have any knowhow about this organization?)
ለቃለ መጠይቅ ፈተና ከመቅረባችሁ በፊት ስለ መስሪያ ቤቱ የምስረታ ዘመን፣ ተልዕኮውን (Mission)፣ አላማውን እና ስፋቱን (Scope and Objective)፣ ራዕዩን (Vision)፣ የምርት ውጤት (Final Output) አስቀድመው ለማወቅ እና እርሰዎ ለአላማው መሳካት የሚያደርጉትነ አስተዋጽኦ ለማካተት ይሞክሩ። ይህንን መረጃ ከድረገጽ እና ከተለጠፉ ታፔላዎች ማግኘት ይቻላል። ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለሥራው ትኩረት መስጠትን ያመለክታል።
Join Our Telegram if You not Joined it Already
Join us on Telegram ስራዎችን በቴሌግራም ለመከታተል ይህንን ይጫኑ
Stay in Touch & Follow us on our Social Media Platforms to Get Latest Updates for Latest Opportunities. Facebook Page
The interested applicants can apply before the closing date of application. For more information please read the full article.
NB: Whenever you are looking for job in Ethiopia, just remember www.harmeejobs.com. We hope that harmeejobs.com will help you find your dream job quickly and easily.
4ኛ. ለምን እዚህ መቀጠር ፈለጉ?
(Why did you want to be employee in this company?)
በምንም ምክንያት “ሥራ ዕድል ስለፈጠረልኝ፣ ደሞዝተኛ ለመሆን፣ ሥራ ላለማጣት” የሚሉ ነገሮችን እንዳትመልሱ። በምትኩ አግባብነት ያላቸውን መልሶች ለምሳሌ ያህል ቀርበዋል። እነሱም:-
~ “በመስሪያ ቤቱ ባሉት ዘርፍ/ዘርፎች ላይ ብሳተፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደማበረክት ስላመንኩኝ”
~ “መስሪያ ቤቱ የላቀ እንቅስቃሴዎችን እያስመዘገበ በመሆኑ እኔም የበኩሌን ድርሻ በመወጣት ሀገሬን እና መስሪያ ቤቱን ማሳደግ ስለምፈልግ፡፡”
~ መስሪያ ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት በመጥቀስ “እንደዚህ ያለ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች ላይ መሆን ታላቅ እርካታን ስለሚሰጠኝ።” ብለው መልሱ።
5ኛ. ለመስሪያ ቤቱ ምን አይነት አስተዋጽኦ አደርጋለሁ ብለው ያምናሉ?
(If you will be employed, what role do you believe that you may pay for company?)
በመስሪያ ቤቱ የምሰራ ከሆንኩ፤ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ የቡድን አንድነትን ማጠናከር (Team Work)፣ የክህሎት ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን ማመቻቸት (Skill Building Trainings)፣ የሥራ ልውውጥ ማድረግ (Experience Sharing)፣ አዳዲስ ጥናቶችን ከመደበኛ ሥራዬ ጎን ለጎን በመስራት (Researches and Projects)፣ ደንበኞችን በአክብሮት እና በተገቢው ሁኔታ ማስተናገድ (Respect and Legality for customers) እና መሰል ነገሮችን በማድረግ ለመስሪያ ቤቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ ተናገሩ።
6ኛ. ጠንካራ ጎኖዎ ምን ምንድናቸው?
(What are your strength?)
የምትፈልጉትን ምኞት ሳይሆን እውነተኛ ጥንካሬዎቻችሁን መስክሩ። ከምትወዳደሩበት የሥራ መደብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሙያዊ ጥንካሬዎችዎን ብታስቀድሙ የተሻለ ነው ፡፡
7ኛ. የዚህን ድርጅት ራዕይ እና ተልእኮ ያውቃሉ?
(What are vision and missions of this organization?)
ይህን ጥያቄ ለመመለስ አስቀድሞ መዘጋጀት ይጠበቅባችኋል። እየተወዳደራችሁበት ያለውን የድርጅቱን ራዕይ፣ ዓላማ እና ተልእኮ አስቀድማችሁ በሚገባ ማወቅ አለባችሁ። ይህንን መረጃ በድርጅቱ ድረገጽ፣ በተሰቀሉ ባነሮች ላይ፣ በታተሙ በራሪ ወረቀቶች ላይ፣ በድርጅቱ የውስጥ ግድግዳዎች ላይ ስለሚገኙ ፈጽሞ ሳታውቁ እንዳትገቡ ይመከራል። ምንም መረጃ ባታገኙ እንኳን ገና ራዕይ እና ተልዕኮ ያልረቀቀላቸው ሊሆኑ ስለሚችሉ በራስዎ ከመመለስ ይልቅ የቅርብ ሰዎችን አፈላልጎ መጠየቅ ተገቢ ነው።
8ኛ. ስለ ድርጅቱ ምን ምን ያውቃሉ?
(What knowhows do you have about this organization?)
እያንዳንዱ ድርጊት የራሱ የሆነ ታሪክ አለው። ይህም ጥያቄ ድርጅቱን ለማወቅ እና የድርጅቱ ሰራተኛ ለመሆን ካላችሁ ጉጉት አንጻር ምን ያክል እንደተጓዛችሁ የሚያመላክት ስለሆነ ሰፋ ያለ መረጃዎችን በማሰባሰብ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው። ለዚህ መልስ ለመስጠት ቢያንስ መቼ እንደተመሰረተ፣ ማን እንደመሰረተው (ባለቤቱ ማን እንደሆነ)፣ የት እና በምን ያክል መነሻ ገንዘብ (Capital) እንደተመሰረተ፣ ስንት ቅርንጫፎች እንዳሉት፣ ዋና መስሪያ ቤቱ የት እንደሆነ፣ ምን ምን አይነት አገልግሎቶች እንደሚሰጥ፣ ምን ያክል የገንዘብ ሃብት እንዳለው፣ ምን ያክል ሰራተኞች እንዳሉት፣ ምን አይነት የእድገት ፍጥነት እንዳለው እና የመሳሰሉትን ማወቅ ይኖርባችኋል። እነዚህን ካወቃችሁ የድርጅቱን ማንነት መግለጽ ትችላላችሁ ማለት ነው።
9ኛ. በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ሊኖሩ የሚገባቸው መርሆች እና እሴቶች ምን ምን ናቸው?
(What are values and principles expected from one organization?)
በአብዛኛው እነዚህ ነገሮች፤ ለሁሉም ድርጅቶች ተቀራራቢ የሆነ ይዘት ቢኖራቸውም እንደ ድርጅቱ ባህርይ እና ይዘት ሊለያዩ ስለ ሚችሉ በራሱ በድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እሴቶች እና መርሆች አፈላልጎ ማወቅ ተገቢ ነው።
ከእነዚህም ውስጥ ሃቀኝነት (Integrity)፣ የደንበኞች እርካታ (Customer Satisfaction)፣ የሰራተኞች እርካታ (Employees Satisfaction)፣ ታማኝነት (Honesty)፣ የቡድን ወይም የኅብረት ሥራ (Team Work)፣ የህዝብን አደራ መወጣት (Public Trust)፣ ትህትና (Humility)፣ ፈገግተኛ መሆን (Simplicity)፣ አንድነት (Unity)፣ ደስተኛነት (Happiness)፣ ነጻነት (Freedom)፣ ግልጸኝነት (Articulate)፣ ፍቅር ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
10ኛ. ድክመቶችዎ ምን ምን ናቸው? [what are your weaknesses?]
…
ለሁሉም ሰው ድክመቶች ቢኖሩበትም ቅሉ በሥራ ቃለ መጠይቅ ወቅት እኒህ እኒህ ድክመቶች አሉብኝ ብሎ መናገር አይመከርም። ይልቁን “የሚታይ ድክመት አለብኝ ብዬ አላምንም ለዚህም ማስረጃ የሚሆነኝ እኔ ባለብኝ ድክመት ምክንያት ነገሮች ተበላሽተውበኝ አለማወቃቸው አንዱ ማሳያዬ ነው” ብሎ መመለስ ተገቢ ይሆናል፡፡
…
11ኛ. በሙያዎ ያስመዘገቡት ስኬት ምንድነው? [what role do you have payed before with your profession?]
…
አሁን ሊቀጠሩበት ባለው የሙያ ዘርፍ ቀደም ብለው ያስመዘገቡትን ውጤት ይናገሩ። የሠሩትን ነገር መናገር።
+++++++++++++++×
++. . ለተመራቂ ተማሪዎች
++. # የቃለመጠይቅ መረጃ [Interview]
—— ——————
የተማሩትን ት/ት በተመለከተ
…
1ኛ。የተማሩበትን የትምህርት ክፍል ባጭሩ ያብራሩል![ለምሳሌ የተማሩት CoTM ትምህርት ክፍል ከሆነ፦ What do you mean by construction, technology and management?]
…
በዚህ ጥያቄ ላይ ለማወቅ የተፈለገው ነገር የት/ት ክፍሉን ስም አይደለም። ይልቁንም ስለትምህርት ክፍሉ ጠቃሚነት፣ ከጊዜ ጥራት እና ኢኮኖሚ አንጻር የሚፈይዳቸውን ሃገራዊ አስተዋጽኦዎች [cost, time and quality]፣ ከሃብት አጠቃቀም አንጻር የሚያበረክታቸውን ዋጋዎች [manpower, material, equipment, natural resourses management]፣ የማህበረሰብን ችግር ከመፍታት አንጻር ያለውን ቦታ [solving role to community problem]፣ ከተማሯቸው የትምህርት አይነቶች ጋር በማዛመድ አጠር እና ግልጽ በሆነ መልኩ ለማስረዳት ይሞክሩ።
….
2ኛ。እርስዎ በተማሩት ትምህርት ያገኙት የብቃት ክህሎቶች ምን ምን ናቸው? [what are your professional skills?]ያለዎትን
….
ለዚህ ጥያቄ ደግሞ ችሎታ በክፍል በክፍል ለማስረዳት መቻል አለብዎት። ለምሳሌ፦
የኮምፒውተር_ሥራ_ብቃት [computer skill]፦ የሚችሏቸውንና የተማሯቸውን ሶፍትዌሮችን {autocad, microsoft project planner, peachtree, archicad, …} እና ማይችሮሶፍቶች {microsoft word, micrososf excel, microsoft powerpoint…} etc
. # ሙያዊ_የሥነዘዴ_ብቃት [Technical skill]፦ የዋጋ ትንበያ {cost estimation}፣ የገበያ ዳሰሳ {market analaysis}፣ የጊዜ ሰሌዳ እና የዕቅድ ሥራ {scheduling and planning}፣ …. etc
. # የሥራ_አመራር_ብቃት [Managemental skills]፦ የቡድን ሥራ {team and group working}፣ሰራተኞችን ማበረታት {motivation}፣ የመሪነት ክህሎት {Leadership}፣ የቁጥጥርና ክትትል ክህሎት {monitoring and controling skill}…. etc
. # ሥነ_ጥበባዊ_ወይም_ሳይንሳዊ_ክህሎት [Scientific skills]፦ ጥናታዊ ምርምሮችን ማከናወን {research}፣ የቴክኖሎጂ ግኝቶች ላይ መሳተፍ {investigation for technological issues}፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም {trying to use new technology outputs}…. etc
. # ሌሎችም
….
3ኛ。ማህበረሰቡን በምን በምን ተጨማሪ ሥራዎች አገለግላለሁ ብለው አስበዋል? [what do you planned to serve the community out of your employeed job?]
….
ይህ ጥያቄ ከሚቀጠሩበት የሙያ ቦታ ወጣ ያለ ሃሳብ ያለዎት ትጉህ ሠራተኛ መሆንዎን ለማወቅ ነው። ለምሳሌ የሚወዳደሩት ለመምህርነት፣ ለቢሮ ሠራተኛነት፣ ለባንክ መኮንንነት ከሆነ፣ ጥያቄው ከዚህ ወጣ ያለ ሃሳብ ስለመኖሩ ለማወቅ ያተኮረ ነው። ስለሆነም ከእነዚህ ሥራዎች ዉጪ የተለያዩ ጥናታዊ ዳሰሳዎችን በማቅረብ {by implementing research for company and local problems፣ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት {community servoce provision}፣ ሙያዊ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት {giving profesional trainings for community}…etc ብለው ቢመልሱ የተሻለ ነው።
….